Original caption
The number of children we have shouldn’t be determined by our confidence in our own ability alone, physically, emotionally, or financially. Parenthood has always required something greater than us. It requires surrender. Psalm 127:1 says, “Unless the Lord watches over the city, the guards stand watch in vain.” In the same way, we can plan, prepare, protect, provide, and do everything within our ability but ultimately, our children belong to God, and we need Him to raise them well. Even becoming a parent is not completely within our control. We can choose intimacy, we can plan for children, or plan not to have them, but we cannot command life into existence. Life itself is a gift from God. So when we ask, “How many children should we have?” maybe the answer isn’t found in a number someone else decided was manageable. It is a question between you, your spouse, and God. For one family, that may be one child. For another, it may be two, five, or more. There is no universally “right” number. Because no number of children is easy when we believe we have to carry the responsibility entirely on our own. Parenthood was never meant to be about proving how much we can handle. It is about faithfully stewarding what God places in our hands and trusting Him with what we cannot carry alone. የምንወልዳቸው ልጆች ቁጥር በራሳችን አቅም ላይ ብቻ በአካል፣ በስሜትም ሆነ በገንዘብ ፣ የተመሰረተ መሆን የለበትም። ወላጅነት ሁልጊዜም ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ነገርን ይፈልጋል። ለእግዚአብሔር መሰጠትንና መታመንን። መዝሙር 127፥1 እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ከተማን ባይጠብቅ፣ ጠባቂው በከንቱ ይጠብቃል።” እኛም ማቀድ፣ መዘጋጀት፣ መጠበቅ፣ ማቅረብና በአቅማችን ያለውን ሁሉ ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን በመጨረሻ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ናቸው፤ በመልካም ሁኔታ ለማሳደግም እርሱን እንፈልጋለን። ወላጅ መሆን እንኳን ሙሉ በሙሉ በእኛ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። ልጅ ለመውለድ ማቀድ እንችላለን፣ ላለመውለድም ማቀድ እንችላለን፤ ነገር ግን ሕይወትን እኛ አንፈጥርም። ሕይወት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ ነው። ስለዚህ፣ “ስንት ልጅ ሊኖረን ይገባል?” ብለን ስንጠይቅ፣ መልሱ ሌሎች ሰዎች “ይህን ያህል ማሳደግ ይቻላል” ብለው በወሰኑት ቁጥር ውስጥ ላይገኝ ይችላል። ይህ በእናንተ፣ በትዳር አጋራችሁ እና በእግዚአብሔር መካከል የሚወሰን ጉዳይ ነው። ለአንድ ቤተሰብ አንድ ልጅ ሊሆን ይችላል፤ ለሌላው ሁለት፣ አምስት ወይም ከዚያም በላይ። ለሁሉም ቤተሰብ የሚሆን አንድ “ትክክለኛ” ቁጥር የለም። ምክንያቱም የወላጅነትን ኃላፊነት በሙሉ በራሳችን ኃይል መሸከም አለብን ብለን ካሰብን፣ ምንም የልጆች ቁጥር ቀላል አይሆንም። ወላጅነት ምን ያህል መሸከም እንደምንችል ለማሳየት አይደለም። እግዚአብሔር በእጃችን ያስቀመጠውን በታማኝነት ማሳደግ፣ እኛ ብቻችንን መሸከም የማንችለውንም ለእርሱ አደራ መስጠት ነው።#fyp #ethiopian_tik_tok #ሀበሻ🇪🇹🇪🇹🇪🇹tiktok #እናት #parenting