Hook

Their other posts in the index, biggest breakout first.
የስራ ኢንተርቪው ላይ ሁሌም የማይቀር አንድ ጥያቄ አለ። እሺ በጣም ጥሩ። እስቲ አሁን ደግሞ ስለ ጥንካሬሽ እና ስለ ድክመትሽ ንገሪኝ። እሺ እንግዲህ ከጥንካሬ አጎንዬል ጀምርልሽ። እኔ በጣም ደስተኛ ሰው ነኝ። ሁልጊዜም በጣም ደስተኛ ሰው ነኝ። እንዲሁም ደግሞ በጣም ፓሽኔት ነኝ፣ ሃርድ ወርከር ነኝ። እንዲሁም ደግሞ ቲም ወርክ ላይ በደንብ ነው ኢንቮልቭ የማደርገው። ብቻ በጣም ብዙ ብዙ ነገር ላይ እኔ በጣም ጎበዝ ሰው ነኝ። ሞር ደግሞ አብረሽ ሰርተሽ ብታየው በጣም በቃ በጣም ጎበዝ ሰው ነኝ። Hardworking Team player Passionate Fast learner በጣም የተለመዱና ሁሉም ሰው የሚላቸው መልሶች ናቸው። በዛ ላይ ደግሞ ሸምድዳችሁ የመጣችሁ ነው የሚመስለው። ታዲያ ይሄን ጥያቄ እንዴት እንመልስ ካላችሁ አንድ ወይም ሁለት ትክክለኛ ጥንካሬያችሁን ምረጡና ከዚህ በፊት የሰራችሁ ስራ ላይ እንዴት እንደተጠቀማችሁት እና ምን ውጤት እንዳስገኘላችሁ በስቶሪ መልክ ንገሯቸው። እሺ ድክመቶቹሽስ? እኔ ትልቁ ድክመቴ በጣም ፐርፌክሽኒስት ነኝ። በቃ ሁሉንም ነገር ስትሰራ ፐርፌክት ካልሆነ ደስ አይለኝም። ይሄ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ ሪኩሩተሮች በጣም የተለቻቸው መልስ ነው። ለስራዬ በጣም ኬር አደርጋለሁ ከልክ በላይ ነው የምሰራው። አንዳንዴ ደግሞ ምንም ድክመት የለኝም የሚሉ መልሶች ኢንተርቪው ለሚያደርጋችሁ ሰው ጥሩ ኢምፕሬሽን አይፈጥሩም። ስለዚህ ትክክለኛ ድክመታችሁን ንገሯቸውና ለማሻሻል እየሰራችሁበት እንደሆነ ንገሯቸው። ያ ማለት ግን ዲስኳሊፋይድ የሚያደርጋችሁን ድክመት ተናገሩ ማለት አይደለም። ከዚህ በፊት አንድ ነገር ስትሰራ ፐርፌክት እስኪሆን ድረስ በጣም ጊዜ ይፈጅበት ነበር። አሁን ግን ከስር ከስር ፊድባክ እየተቀበልኩኝ በመስራት ይሄንን ድክመቴን እንዲያሻሻልኩ ነው። ይሄ ቪዲዮ ለቀጣይ ኢንተርቪውያችሁ ስለሚጠቅማችሁ ሴቭ አድርጉት። በየሳምንቱ እንደዚህ አይነት ከሪየር ቲፖች እንዲደርሷችሁ ከፈለጋችሁ ደግሞ ፎሎ አድርጉት።