Hook

Their other posts in the index, biggest breakout first.
ለምንድነው የሥራ ኢንተርቪው ላይ እንግሊዝኛ የሚከብደን? ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ሰው የስራ ኢንተርቪው ፌል የሚያደርገው ታለንቱ ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን በእንግሊዘኛ ቋንቋ በደንብ ራሱን ኤክስፕረስ ማድረግ ስለሚከብደው ነው። በዚህ ምክንያት ኢንተርቪው ላይ ትክክለኛ ፖቴንሻላችሁን ለማሳየት ስትራግል የምታደርጉ ከሆነ ማድረግ ያለባችሁን እና የሌለባችሁን እነግራችኋለሁ። በደንብ አዳምጡ። አንደኛ ኢንተርቪው በራሱ ነርቨስ ያደርገናል። ከዛ ቋንቋ ደግሞ ሲጨመርበት አስቡት። አእምሮአችን ከዛ ሲቹዌሽን ቶሎ መውጣት ስለሚፈልግ ሳናስበው ቶሎ ቶሎ ለመናገር እንሞክራለን። ከዛም የምናውቀው ራሱ ይጠፋብናል እና መንተባተብ እንጀምራለን። ስለዚህ በእንደዚህ አይነት ሰዓት ቀስ ብላችሁ እና ተረጋግታችሁ ለመናገር ሞክሩ። ይሄ ደግሞ በራስ መተማመን እንዳላችሁ ያሳያል። ሁለተኛ ደግሞ በጭራሽ ማድረግ የሌለባችሁ ነገር ኢንተርቪው ላይ ለምትጠየቁት ጥያቄ መልሶችን ሸምድዳችሁ መምጣት። አስቡት ኢንተርቪው ላይ ከሸመደዳችሁት ውስጥ አንድ ቃል እንኳን ብትረሱ በድንጋጤ ሙሉ ለሙሉ ነው የሚጠፋባችሁ። ስለዚህ ግጥም አድርጋችሁ ከመሸምደድ ይልቅ ዋና ዋና መናገር አለብኝ ብላችሁ የምታስቧቸውን ነጥቦች በቃላችሁ ይዛችሁ ኢንተርቪው ላይ በራሳችሁ አገላለጽ ብታቀርቡት ሞር ኦተንቲክ ይመስላል። ሶስተኛ ደግሞ ኢንተርቪውየሩ የሆነ ጥያቄ ጠየቃችሁ። ለዛ ጥያቄ መልሱን ታውቁታላችሁ ግን በእንግሊዘኛ እንዴት እንደምታብራሩ ግራ ገባችሁ። ስለዚህ በዚህ ሰዓት ዝም ከመማል ይልቅ ቆይ። መልሱን አውቀዋለሁ ግን በደንብ ኤክስፕሌይን ለማድረግ ቃላት ለማሰብ ልሞክር ብላችሁ ትንሽ ታይም እንዲሰጧችሁ ማድረግ ዝም ከመማል በጣም ይሻላል። እንደውም እንደዚህ አይነት መልስ ከሰጣችሁ ኢሞሽናሊ ኢንተለጀንት እንደሆናችሁም ያሳያላችኋል። እነዚህ ብቻ አይደሉም። ሌሎችንም በጣም ብዙ ከቋንቋ ጋር የተያያዙ ኢንተርቪው ላይ ሊጠቅማችሁ የሚችሉ ብዙ ቲፖች አሉ። ቀጣይ ክፍል እንድንሰራላችሁ ከፈለጋችሁ ኮሜንት ላይ ፓርት ቱ ብላችሁ አስቀምጡልን። የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታችሁን ደግሞ በደንብ ማሻሻል ከፈለጋችሁ ከነቢል ኢሜይል ጋር በመሆን የእንግሊዘኛ ኮርስ አዘጋጅተናል። ባዮ ላይ ባለው ዌብሳይት ገብታችሁ መማር ትችላላችሁ።