Hook

Their other posts in the index, biggest breakout first.
ሰላም ሁኑ የትኛዋ ቲክቶከር መቅዲ ምን ልማድ እያደረገች ነው? ብዙ ሰዎች እሷ በምትለቀው ኮንተንቶች ሁለተኛ ሚስት መሆኗን ይፋ ማድረጓ ትንሽ የደበራቸው ይመስላል። ነገር ግን እሷ ኢንቴንሽኗ ሁለተኛ ሚስት መሆኗን ለማሳወቅ ነው ወይስ ሌላ ነው? አስተውላችሁ ከሆነ እያንዳንዱ ሁለተኛ ሚስትነቷን ጠቅሳ ወይም ባሏን ጠቅሳ የምትሰራቸው ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያ አለ። እንደዛ የምታደርገው ደግሞ ሁም ብላ ነው። ሁለተኛ ሚስትነት በእኛ ሶሳይቲ ውስጥ ትንሽ ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ ይሄ ኦድ የሆነ ነገር እንደ ሁክ ወይም ደግሞ የሰውን ጆሮ እንደ መያዣ መጀመሪያ ላይ ትጠቀማለች። ከዛ በኋላ ማስታወቂያዋን ለማስተላለፍ በጣም ቀላል ይሆንላታል ማለት ነው። ስለዚህ እናንተ መቀየር በማትችሉት ነገር ከምትጨነቁ እንዴት የራሳችሁን ፕሮዳክት ወይም ሰርቪስ የሰውን ጆሮ በሚስብ መልኩ ማስተዋወቅ አለብን የሚለውን ነገር ከሷ ትንሽ ብትማሩና እሱን ነገር በደንብ ፎከስ አድርገን ብናየው የራሳችንን ፕሮዳክት ወይም ሰርቪስ ለመሸጥ እንጠቀምበታለን። እኔ በምሰጠው ኮንተንት ክሪኤሽን ክላስ አንደኛው የምትማሩት ስቶሪ ቴሊንግ ወይም እንዴት አድርጋችሁ ስቶሪ መናገር እንዳለባችሁ መጀመሪያ ቪዲዮችሁን ስትጀምሩ እንዴት የሰዎችን ጆሮ አይን መያዝ እንዳለባችሁ እሱን ትማራላችሁ። አሁን የቪዲዮዬ መግቢያ ላይ እራሱ የመቅዲን ወይም የሚስ ሹገርን ስም መጥራቴ የምትጠቀማቸውን የማርኬቲንግ ስትራቴጂዎች እናንተም ልብ ብላችሁ እንድታዩት ስለፈለኩ ነው። እናንተም በራሳችሁ ኮንተንት መምጣት የምትፈልጉ ከሆነ ሙሉ የኮንተንት ክሪኤሽን ክላስ ኤዲቲንግ ፊልሚንግ እና ስቶሪ ቴሊንግን ጨምሮ ሁለተኛ ዙር ምዝገባችንን ስለጀመርን አሁኑኑ ባዮ ላይ ባለው ስልክ እየደወላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። በራሳችን ቢዝነስ ቢዚ ብንሆን ይሻለናል።